ቴዲ አፍሮን የሚወዱት ሰዎች እጅግ በርካታ የመሆናቸውን ያህል ጥቂት የማይባሉ ደግሞ አምርረው ይጠሉታል። ደጋፊዎቹ በተለይ በዘመነ ትህነግ በድፍረት የሚያዜማቸውን እያነሱ “የአንድ ሰው ሠራዊት” ይሉታል። የሚጠሉት ደግሞ ቴዲ “ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?” ቢል እንኳን “ይሄ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ፣ …” በማለት የስድብ ናዳ ያወርዱበታል። ቴዲ በትህነግ ዘመን ግልጽ ግፎች ደርሰውበታል። የሙዚቃ ኮንሰርቶቹ ያለ ምንም ካሣና ቅድመ ማስታወቂያ ቲኬት ከተሸጠ በኋላ በተደጋጋሚ ተሰርዘውበታል። የጎዳና ተዳዳሪ ገድለሃል በሚል ክስ ለእስር በተዳረገበት ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበ ቁጥር ያለማቋረጥ እያለቀሰ ንጹሕ መሆኑን ለማሳመን ሞክሯል። ከእስር የተለቀቀበት አግባብም በራሱ ብዙ ሊያስብል የሚችል ነው። በአገራችን የለውጥ መዓበል በተነሳበት ወቅት ጃዋርን ጨምሮ አክራሪና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች … [Read more...] about “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል። በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል። በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና … [Read more...] about የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ
በኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዷል። ተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ተሳትፈዋል። የምርጫው ሒደት ባብዛኛው ከተጽዕኖ የራቀ ነው ሊባል ይችላል። ተቃዋሚዎች በቂ የአየር ጊዜ ተሰጥቷው ፕሮግራማቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ተደርገዋል። በርካታ ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ተካሂዷል። ለገዢው ፓርቲ እንደ በፊቱ ጊዜያት ፕሮፓጋንዳውን እንዲያሰራጭ እጥፍ ጊዜ አልተሰጠውም። ከተቃዋሚዎቹ እኩል በሚባል መልኩ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ነው የተደረገው። ከሁሉ በላይ በደኅንነቱ መሥሪያ በጀት ተበጅቶለት ኮሮጆ ለመገልበጥ የሚሠራ ኃይል የለም። ምርጫ ቦርድም ነጻና ተዓማኒነቱን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። በምርጫው ቀን መራጩ ሕዝብ ነጸ በሚባል መልኩ ሲመርጥ ውሏል። በተለይ በከተሞች አካባቢ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚያስብል ተግባር እንዳልተፈጸመ ታይቷል። … [Read more...] about ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ
ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
ቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጃል መሮ በሚል ስም የሚታወቀውን ሽፍታ ሽፋን ሲሰጠው ስለምንነቱና በትክክልም እሱ ስለመሆኑ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። በቢቢሲ አማርኛና በቪኦኤ እንዳሻው ጊዜ መርጦ ወንጀሉን የሚያስተባብለው ጃል መሮ፤ ሲያሻው የሰጠውን ቃለ ምልልስ ስልክ ደውሎ እንዳይተላለፍ የሚያዝ ለመሆኑ ናኮር መልካ “ጃል መሮ ቃለ ምልልሱ እንዳይተላለፍ በጠየቁት መሠረት ትቼዋለሁ” ሲል ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ … [Read more...] about ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
ለትምህርት እንዲሆነን
ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!
መስከረም 20፤ 2013 ዓም የትውልድ ዋርካ፤ የዘመናት ዕንቁ የሆኑትን የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም ማረፋቸው ተሰምቷል። ስለ እርሳቸው ብዙ ማለት ይቻላል። ሞት ለማንም የማይቀር ቢሆንም ስለ እርሳቸው ዕረፍት እኛ ከምንናገረው በላይ ራሳቸው ስለ ሞት የተናገሩትን አትመነዋል። ከሁሉ በላይ “ዛሬም እንደ ትናንት” የተሰኘውን የመጨረሻ መጽሐፋቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት አሳትመው ማረፋቸው ለአገራቸው እስከመጨረሻው የተጉ የዘመናችን ዕንቁ! የኔታ መስፍን! የቅኔ ጌታ! የዕውቀት ገበታ! ቢባልላቸው በፍጹም የሚያንስባቸው አይደለም። የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ ጥር/2009 ስለራሳቸው ህይወትና ጻዕረሞት የጻፉትን በድጋሚ በማተም የስንብት ሐዘናችንን እንገልጻለን። ለቤተሰብ፣ ለዘመድ፣ ለወዳጅ፣ ለመላው የአገራችን ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን። ጎልጉል የድረገጽ … [Read more...] about የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!
“ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
የሙያው ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ታጋቾችን ማስለቀቅ ራሱን የቻለ ታላቅ ጥበብና ስልት ይጠይቃል ይላሉ። የአጋቾችን ስነልቡና ለመስረቅ፣ ለማለስለስ፣ ወዘተ አደራዳሪዎች ፈጽሞ ሊታሰቡ የማይችሉ የሚባሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። የአጋቾቹን ፍቅረኛ ወይም እናት ወይም ሌላ ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወደ ዕገታው ቦታ በማምጣት በድምጽ ማጉያ የተማጽንዖ ቃል እንዲናገሩ ይደረጋሉ። የሃይማኖት መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ሌሎች ተጽዕኖና አመኔታ ሊጣልባቸው የሚችሉ ሰዎች በዚህ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ይህንና ሌሎች መሰል ተግባራትን በመጠቀም የታገቱት ያለ አንዳች ችግር በነጻ እንዲወጡ ሙከራ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ዕገታ በሰላም የመጠናቀቅ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይባላል። ማፈን፣ ማገት፣ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው በቁጥጥር ሥር ማዋል፣ ወዘተ ያልተለመደ ተግባር … [Read more...] about “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
የኖቤል የሰላም አሻራ በኤርትራም! ባስቸኳይ!
የ2019 የዓለም የኖቤል የሰላም ሽልማት የእኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የእኛው ቤተሰቦች የሆኑት የኤርትራዊንም ነው ሲባል ለጎልጉል የሚገባው ሃሳቡ ወይም ንግግሩ ከመደመርም በላይ የሚታይ ስለሆነ ብቻ ነው። እንደሚታወቀው የኖቤል ተሸላሚዎች ከሚቀበሉት ዲፕሎማ በተጨማሪ ግምቱ 10ሺህ ዶላር የሚገመት 18 ካራት አረንጓዴ ወርቅ የተለበደበት 24 ካራት ወርቅ የሚሰጥ ሲሆን ወደ 950ሺህ ዶላር የሚገመት የገንዘብ ሽልማትም አብሮ ይሰጣል። ከገንዘቡና ከወርቁ ይልቅ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ዝናው ከሁሉ የሚበልጥ ነው። ከዚህ በፊት በተለያዩ መስኮች የተሸለሙ በተሰጣቸው ገንዘብ ምን እንዳደረጉበት ሲናገሩ ለልጆቼ ኮሌጅ ወጪ አዋልኩት፤ አዲስ ቤት ገዛሁበት፤ በቀጥታ ወደ ቁጠባ የባንክ ሒሳቤ ነው አስገባሁት፤ ወዘተ የሚሉ መልሶችን ሰጥተዋል። የ2019 የዓለም የሰላም ሎሬት ዐቢይ … [Read more...] about የኖቤል የሰላም አሻራ በኤርትራም! ባስቸኳይ!
የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው። ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች … [Read more...] about የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ተመልሰናል!
የጎልጉል ርዕሰ አንቀጽ በቅድሚያ ለጎልጉል ወዳጆችና አንባቢያን እንዲሁም ጠላቶች ለመጥፋታችን በርካታ አጥጋቢ ምክያቶች ቢኖሩንም በቅድሚያ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። መረጃ ከእኛ ለማግኘት ፈልጋችሁ ለበርካታ ወራት ሳታገኙ በመቅረታችሁ እናዝናለን። “የት ጠፋችሁ?” በማለት በተደጋጋሚ ስትጠይቁን ለነበራችሁ ቅኖች ምስጋናችን የላቀ ነው። የእናንተን መሰሉ ቅንነት ወደፊትም በብርታት እንድንቀጥል የሚያደርገን ነውና መልካምነታችሁ ወደፊትም አይለየን። በመጥፋታችን ደስ ብሏችሁ የነበረ የበለጠ ደስ ይበላችሁ እንደወጣን አልቀረንም፤ መጥተናል። አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ስንመለከተው በርካታ ተስፋ ሰጪ ተግባራት ሲደረጉ ብንመለከትም ያንን የሚያፈርስ እኩይ ተግባር ሲፈጸምም እናያለን። የተደፈውን ቀዳዳ መልሰው የሚቆፍሩ ክፉዎች የመኖራቸውን ያህል ላገራቸው ምንም ጩኸት ሳያሰሙ … [Read more...] about ተመልሰናል!