• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ጣጣ የለውም!” ሌላው ግሽበት

September 14, 2012 06:11 am by Editor 3 Comments

(ቀጭኑ ዘ-ቄራ )

ዛሬ ዛሬ ባገራችን በተለይም አዲስ አበባ በየቀኑ የሚመረቱት ቃላቶች የሚሰበስባቸው ቢገኝ አንድ ራሱን የቻለ ቋንቋ ይመሰርታሉ። ለተረብ የሚወረወሩት ቃላቶች ደግሞ ፈጠራቸው እስኪገርም ድረስ ያንተከትካሉ፤ ያስቃሉ። ወሬ ከሚፈላባቸው ቦታዎች መካከል ጫት ቤቶች ይጠቀሳሉ። በጫት ቤት ወሬ ይበለታል፤ መንግስት ይገሸለጣል። ጫት ቤት ሆነው ከፍተኛ መመሪያ የሚያስተላልፉ ጥቂት አይደሉም። ጫት ቤት ቁጭ ብለው መንገድ እንዲወጠር የሚያዙ የፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎች አሉ። ከአቶ መለስ ጠባቂዎችም መካከል መርቃኞች የነበሩ፣ ለስራ ሲፈለጉ ሸሚዝ ቀይረው በኮብራ የሚበሩ አሉ። ጫት ቤት የማይሰበስበው ሰው የለም። ዶክተሮች፣ የህግ ሰዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ልማታዊ የህዝብ ግንኙነቶች፣ ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ የደህንነት ሰዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ ከንቲባዎች፣ ዞንና የቀበሌ ሰራተኞች… ምን አለፋችሁ ኢህአዴግ ውስጥ የአባልነት አንዱ መስፈርት ጫት መቃም ይመስላል።

አንዴ የዱከም ከተማ በድንገት ሺሳ ቤቶችን ለመዝጋት አሰሳ አደረገ። አሰሳው ከተጠናቀቀ በኋላ ሪፖርት ሲቀርብ በሺሻ ቤቶች ውስጥ ጫት እየበሉ ሺሻ ሲያጨሱ ከነ አመዳቸው ከተያዙት መካከል አብዛኞቹ የከተማዋ አስተዳደር ሰራተኞች፣ መሃንዲሶች፣ የጸጥታ ሰራተኖችና ባለሃብቶች ነበሩ። ታስረው ከቆዩ ስራ ሊቆም ስለሆነ እንዲፈቱ ተወስኖ አፋቸውን ተለቃልቀው እየተሳሳቁ ወደ ቢሮ ሲገቡ ሰውም እየሳቀ እንደተቀበላቸው አስታውሳለሁ። አዲስ አበባም ተመሳሳይ አጋጣሚ ተስተውሎ ነበር። እንደው ስለ ግሽበት ለመናገር ለመንደርደሪያ ያህል ይህንን አልኩ እንጂ የጽሁፌ አላማ ሌላ ነው። ወደፊት ግን ሁሉንም እየበተንኩ በጎልጉል አማካይነት ለማስነበብ ቃል እገባለሁ። እንግዲህ ካልተነቃብኝ ወይም “ጣጣ የለውም” እያላችሁ ካላጋፈጣችሁን ማለት ነው።

ጎይቶምን የማውቀው ከአንድ የጫት ማስቃሚያ ቤት ውስጥ ተጠግቶ እየተላላከ ነበር። በወጉ የማይበላ፣ የሚተኛበት ያጣ ፣ የሚረዳው ወገንና ዘመድ የሌለው ባዶውን ያለ ሰው ነበር። በ1997 ጋዜጠኞች ተሰባስበው በሚቅሙበት ጫት ቤት ተጠግቶ የማውቀው ሰው በድንገት መሰወሩን ሰማሁ። የጎይቶምን መሰወር የሰሙ ለጊዜው በድንጋጤ ሃዘናቸውን ከመግለጽ ውጪ አማራጭ አልነበራቸውም። ቆይቶም ተረሳ፤ ጎይቶም የገባበትን የሚያውቅ ግን አልነበረም።

ከጎይቶም መጥፋት ጋር አያይዞ አንዱ ጓደኛችን በጥርጣሬ ብዙ ነገሮችን ቢናገርም አድማጭ ማግኘት አልቻለም ነበር። በነገራችን ላይ ጫት ቤቶች ውስጥ አብዮታዊ ዲሞክራሲን፣ አቶ መለስንና ሼኽ መሃመድ ሁሴን አላሙዲን የሚሰብኩ በጀት የሚመደብላቸው አሉ። በጫት ቤት ኢህአዴግን የማስረጽ ሚና ያላቸው እኒህ ሰዎች ስለሚታወቁ፣ ጫት በባህሪው ደግና ለስላሳ ስለሚያደርግ አይፈሩም ነበር። እንደውም ከቆይታ በኋላ እነሱ ዜና አቀባይ በመሆን ጋዜጠኞችን ይረዱ ነበር። ወደ ጎይቶም እንመለስ…

በግምት ከስድስት ወር በኋላ ቦሌ ጌቱ ገለቴ ህንፃ ዌስተርን ዩኒየን ቢሮ ውስጥ ያየሁትን ማመን አቃተኝ። ጎይቶም ፊቱ በድሎት አብጦ፣ የወርቅ ሃብልና የእጅ ሰንሰለት ሠንሠለት ደርድሮ ፊቴ ቆሞ ይስቃል። ተሳሳምን። እየሳቀ ጤናዬን ጠየቀኝ። ወዴት እንደምሄድ ከነገርኩት በኋላ ተያይዘን ወጣን። ከህንጻው ፊትለፊት ካቆመው ውብ ላንድ ክሩዘር መኪና ውስጥ እንድገባ ጋበዘኝና ወደ ጉርድ ሾላ ወሰደኝ። መኪናውን እየነዳ በፈገግታ እያየኝ ያወራል። ካልዲስ ቡና ጋብዞኝ ብዙ ሃሳብ ከሰጠኝ በኋላ ተለያየን። መደዋውል ጀምረን ነበር ሳይቆይ ግንኙነታችን ቆመ። እንደሚመስለኝ የጎይቶምን ስልክ ምግብ ይገዙለትና ይረዱት ለነበሩ የጫት ቤቱ ታዳሚዎች መስጠቴ ሳይረብሸው አልቀረም።

ጎይቶም እንደነገረኝ የሁመራ ሰሊጥ ወደ ውጪ የሚልክ ኤክስፖርተር ሆኗል። ባያብራራልኝም እንደተረዳሁት ስሙን ያልገለጸልኝ ተቋም ለሱና ለስድስት ተጨማሪ ሰዎች ስራውን አመቻችቶ፣ ብድር ሰጥቶ፣ አደራጅቶ አሰማርቷቸዋል። አጀብ ነው። ሁለት ዓይነት ዜጎች ማለት ከዚህ ሌላ ምን ሊባል ነው? “ጣጣ የለውም ” ኤክስፖርተሮችና ድንጋይ ማንጠፍ ብርቅ የሆነባቸው እኩል ያለቅሳሉ። እናቱ የሞተችበትና ሚስቱ ውሃ ልትቀዳ ወደ ምንጭ የወረደችበት እኩል አነቡ፤ ተረት ተረት፤ ግን ጣጣ የለውም…

መድሃኔ ሰሜን ሆቴል አካባቢ ይኖራል። በ1997 ዓ ም አዲስ አበባ ሲመጣ አገረ ሰብ ጫማ አድርጎ፣ ቁምጣ ለብሶ ሲሆን እንግድነት ከመጣበት ቤት ደጅ ቆሞ ጥርሱን ሲፍቅ ነበር የሚውለው። አምባሻ ሲገምጥና የትግርኛ አማርኛ ሲናገር ያስቃል። አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በራሱ ስም የተመዘገበ ቦቴ እየነዳ ሰፈር መምጣት ጀመረ። እንግድነት የመጣበት ቤት ከሰል ሲያወርድ የሰፈሩ ጎረምሶች ከመድሃኔ ከሰል ያወረዱበትን ሳንቲም ይቀበሉና አመስግነው ይለያያሉ። “ይህም ጣጣ የለውም” የሚባል የኑሮ ክስረትና የሁለት ዓለም ሰዎች የተጨበጠ ወግ ነው። ግሽበት!!

እንዲህ ያሉትን ታሪኮች ከየት አገኘሃቸው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ግልጽ ላድርግ። ጋዜጠኞች አዘውትረው በሚሰባሰቡባት የወሎ ሰፈሯ ጫት ቤት እድምተኛ እያለሁ የማይጻፉ ትዝብቶች ለውይይት ይቀርቡ ነበር። ብዙ ዘግናኝ ታሪኮች ጫት ቤት ተወቅጠው፣ ጫት ቤት ይቀበራሉ። እነዚህን ታሪኮች በማስታወሻ የሚያስቀምጡ ያልጀዘቡ የጫት ተጠቃሚዎች አሉ። ከነሱ መካከል ነኝ መሰል ለዛሬ ያቀረብኩትን ጽሁፍ ማስታወሻዬ ላይ ለማኖር ችያለሁ።

ውይይቱ የተነሳው ከላይ በርዕስ እንደጠቆምኩት “ጣጣ የለውም፣ አቦ ይመችህ፣ ጭሱ፣ ነብሱ…” የሚሉ ታዳጊ አገር ተረካቢዎች የፈሉትን ያህል ባንድ ጀንበር ሚሊዮኔር የሚሆኑ ህጻናትን የመብዛታቸውና ምንጫቸውም አንድ አካባቢ መሆኑን እንደ ቀልድ ያስተዋሉና ልዩነቱ ያስገረማቸው አዲስ አበባ በየመንገዱ የሚታዩትን ቋሚ ንብረትና ግለሰብ በመጥራት ሲዘረዝሩ አንዱ አንዱን እየተቀበለ ከምርቃና ጋር አጀንዳው ልብ የሚስብ በመሆኑ ነበር።

“ዘጋ፣ ጠረቀመ፣ ቆለፈ፣ ተተኮሰች፣ አመለጠች፣ ሱቅ በረገደች፣ ኮቴ ቀየረች፣ መኩ ሸመተች… ” የሚል ትውልድ መብዛቱን ያስተዋለ አንድ ጋዜጠኛ “ሰው ተራራቀ” የለበት የድምጽ ንዝረት ዛሬ ድረስ አይረሳኝም። ነብሱን ይማረውና ዋሲሁን የሚባለው ጓደኛችን በተደጋጋሚ የሚያነሳውን ሃሳብ አስታወስኩት። እንዲህ ይል ነበር።

በቀለ ሞላ ቢሯቸው ሲገባ ሊስትሯቸው ፊት ለፊት ተሰቅሎ ይታያል። መነሻቸውም መድረሻቸውም ግልጥልጥ ያለ ነው። በሳቸው ወቅት ከሊስትሮ፣ ከሱቅ በደረቴ፣ ከጠጅ ቀጂነት፣ ከበሬ ነጂነት፣ ከቆዳ ገፋፊነት፣ ከጉሊት ቸርቻሪነት…. ተነስተው ትልቅ ደረጃ የደረሱ ብዙ ናቸው። ዘመኑ ተቀይሮ ፣ የግድ ሊስትሮና ጠጅ ቀጂ መሆን ግዳጅ ባይሆንም፣ ትውልዱ ዓይነ ልቡናው በገንዘብ ታውሮ “እገሌ ዘጋ እኔም መዝጋት አለብኝ” በሚል እሳቤ ገንዘብ የሚያስገኝ ከሆነ ማንኛውም ስራ ያለ ህሊና ወቀሳ፣ ለመስራት የመስማማቱን ጉዳይ “የህሊናና የማህበራዊ እሴቶቻችን መገሸብ ውጤት ነው” ነበር ያለው። በተለይም ሼኽ ሞሃመድ ሁሴን አላሙዲን በይፋ አርቲስቱንና ስፖርተኛውን እየሰበሰቡ መንዳት ከጀመሩ በኋላና ኢህአዴግ ከዘረጋው ኢትዮጵያዊ እሴቶችን የማጥፋት ዘመቻ ጋር ተዳምሮ ዋሲሁን የሚለው ግሽበት የአገራችን ታላቅ ስጋት ሆኖ ይታየኛል።

“ባለ ራዕዩ መሪያችን አምራች ዜጎች ስራ አይመርጡም” ብለዋል እየተባለ ኮብል ድንጋይ ሲፈልጡ የሚታዩት የማህበረሰብ ክፍሎች በስራ የማመንና ስራ አለመናቅን የሚያመለክቱ መሆናቸው ባያከራክርም፤ በአገሪቱ አብዛኛው አምራች ዜጋ በድህነቱና በስጋዊ ፍላጎቱ በማታለል ኢትዮጵያዊ ባህሉን እያጣ “ጣጣ የለውም” የሚል የደነዘዘ ትውልድ እንዲሆን ሆን ተብሎ እየተደረገ ነው። አጭር ምሳሌ – አንድ ወጣት እናቷን፣ ወንድሟን፣ አባቷን ወይም የቅርብ ወዳጆቿንና ዘመዶቿን አሳልፋ የምትሰጥ ከሆነች ማህበራዊ መስተጋብሯ ሙሉ በሙሉ ገሽቧል ማለት ነው። ዓይነ ልቡናዋ ተደፍኗል ማለት ነው። ለመኖርም ይሁን ለእለት ከርስ ሲባል የቤተሰብ ትስስርና ፍቅር ተንዷል። እንዲህ ያለ ዜጋ ወደፊት ላገር ምን ይጠቅማል? ትልቅ ገንዘብ ካገኘ አገሩን አሳልፎ ከመስጠት ወደኋላ የሚል አይሆንም።

ኢትዮጵያዊነትን “አየር ላይ ያለ ባዶ መጠሪያ” የሚለው ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የአገሪቱን ባህላዊ እሴቶች እየበላ የጨረሰው፣ የወጉና የባህሉ መጠበቂያ የሆኑትን የሃይማኖት ተቋማቱን በካድሬ ጠቅጥቆ የያዘው፣ የማህበራዊ ተቋማትን ከስለላ መዋቅሩ ጋር ያዋቀረው፣ አዲሱ ትውልድ ሊያውቅ የሚገባውን የአብሮነትና የመተሳሰብ ባህል እያወደመ ባህልም፣ ታሪክም አልባ አስመስሎን የራሱን “ፋልሴቶ” ታሪክ የተጋቱ ትውልድ ለመፍጠር ነው።

ስለ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ በዝርዝር በቀጣይ እመለስበታለሁ። ለዛሬው ግን ከአዲስ አበባ ወደ ሞጆ ሲጓዙ መንገድ ዳር ባለ አንድ አብረቅራቂ ሆቴል እህቶቻችንና ባለትዳሮች አንዴት እንደሚረክሱ ጠቆም አድርጌ አልፋለሁ። በተለያዩ እድሜ ክልል ያሉ ሴቶች በአልባሽ ዘንጠው ወደዛ ያመራሉ። ከድሃ ህዝብ ላይ የሚዘረፍ ገንዘብ ያሳበዳቸው “ሃብታሞች” ጉያ ስር ይሸጎጡና የትውውቅ ስነስርዓት ይከናወናል። የውሽሞች ቀን! አንዱ የሌላውን ውሽማ እንዳይነካ የሚደረግ ጥንቃቄ መሆኑ ነው። የተከበረች የልጆች እናት ቤት ተቀምጣ ለውሽማ ጥንቃቄ። ታዲያ እዚህ የትውውቅ ስነ ሰርዓት ላይ የአሽከርነት ስራ የሚሰሩ ሚስቶቻቸውን ሳይቀር አስዘንጠው ለጨረታ ያቀርባሉ። ባህላችን፣ ፈሪሃ ልቡናችን መገሸቡ ከዚህ በላይ እንዴት ሊገለጽ ይችላል።

በመድሃኒት ሃይል የሚንቀሳቀሱ ሃሺሻሞች፣ አልኮል ጠረናቸውን የቀየረው ሱሰኞች፣ በቀለም ስቱኮ ተደርገው የሚታዩ ርካሾች ህጻናትን ይገዛሉ። ያሉበት ድረስ ያስግዙዋቸዋል። ይህንን ስራ የሚሰሩ ደላሎች የከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ናቸው። እንደ ምግብ በሜኑ ህጻናት የሚቀርብላቸው ባለስልጣናትም አሉ። አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚኖሩ ወገኖች ይመሰክራሉ… ዛሬ በየቦታው በዝግ የሚሰሩ በርካታ አሳፋሪ ተግባራቶች አሉ። በቸር ከከረምን በዝርዝር እናየዋለን። “ጣጣ የለወም!” ለዛሬ እንደመተዋወቂያ በገርድፉ እንጀምር ብዬ ነውና ሃሳቤን ከያዛችሁልኝ የወሬ ቋቱ ነኝና እጥፋለሁ።

ግን አንድ ነገር እዚች ላይ አከል ላድርግ – ይቅርታ ይደረግልኝና ትግራይ ለምን ጫት አይፈቀድም? ነፍሳቸውን ይማረው ለማለት ደረስን ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ ይህንን ጥያቄ ተጠይቀው “ከጫት የምናገኘው ገቢ ቀላል አይደለም” በማለት በሌሎች ክልሎች ጫት “እንዲበላ” በትግራይ ግን ወጣቶችን እንዳያበላሽ ጫት ውግዝ መሆኑን በሾርኔ ተናገሩ። ያለ ስራ ጫት እየበላ እንዲጀዝብ የተፈረደበት ትውልድና ለወደፊት ህይወቱ ሃብት እየተሰነቀለት ያለ ትውልድ አንድ ላይ ይኖራሉ። ለወደፊት የሚጠቅሙ ቁልፍ ተቋማት የሚገነባላቸው ዜጎችና አዲስ ቀርቶባቸው የቀድሞው ንብረታቸው በሃራጅ ለሌሎች የሚተላለፉባቸው ወገኖች ሁሉም አገር አለን ይላሉ። እኩል መሪ ሞተብን ብለው አለቀሱ ተብሎ ባህላችንና ወጋችን ተጣቅሶ ይሰበካል።

አስመጪና ላኪዎች፣ ህንጻ ሚገነቡ፣ ዘመናዊ መኪኖችን የሚያስመጡና የሚሸጡ፣ የፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት የሆኑ፣ የዋና ዋና ካፌ ቤቶችና ንግድ ቤቶች ባለቤት የሆኑ ጥቂቶች ያሉትን ያህል ጎዳና ላይ ወድቀው ከቆሻሻ ላይ የሚመገቡ ብዙሃኖች ናቸው። በሚያስገርም ፍጥነት የጥቂቶች የኢኮኖሚ ጥገኛ ለመሆኑ የሚሮጡ አብዛኞች ባርነትን፣ የነዋሪዎች አኗኗሪና ተመልካች መሆንን “ጣጣ የለውም” በሚል ተቀብለው ለመኖር የተስማሙ ይመስላሉ። ኩራትና ክብር የሆነውን በራስ መተማማን የሞላበትን ባህላቸውን አራግፈው ጥለው የሚዘርፋቸውን ድርጅትና ለባርነት እያዘጋጃቸው ያለውን ተቋም “ይመችህ” ብለው ማሞካሽትን የበለጠባቸው ይመስላሉ።

ድንጋይ ማንጠፍ ትልቅ ስራ ቢሆንም ድንጋይ ለማንጠፍ መታደል የስኬት ሁሉ ውጤት ተደርጎ ዘር እየለዩ ለስራና ለእለት ጉርስ ሲሉ ደረት የሚደቁ ትውልዶች የደራሽ ያለህ ይላሉ። “ጣጣ የለውም” ታላቅ ግሽበት ነውና ማህበራው ቀውስን ለመታደግ ጣጣ የለውም የሚሉ ትውልዶች “ያገባኛልን” ያነግቡ ዘንድ እንትጋ። የመረጃ ማስተላለፊያው ካላሳበቀብኝ በስተቀር በጎልጉል አማካይነት እንገናኛለን።

*******************************************************************************************

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. tinkisu says

    September 15, 2012 01:01 am at 1:01 am

    you guys should to make page share able so that other may got a chance to read the article and to come to your page

    Reply
    • Editor says

      September 15, 2012 02:07 am at 2:07 am

      Thanks tinkisu – we will make a note of that.

      Reply
  2. በለው ! says

    October 26, 2012 05:11 pm at 5:11 pm

    ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተሰምቶህ ለሕዘቦች እኩልነት አብሮ ማደግ ሰላም ፍቅርና መተሳሰብ ዘላቂ እንዲሆን ያሉትን ውስጣዊ ችግሮች እና ውስብስብ የመልካም የአስተዳደር ብልሹነት”ጣጣ አለው” ስትል ለታዘብከው እጅግ ከፍ ያለ ምስጋኔዬ ባለህበት ይድረስህ!። ይመችህ እላለሁ! ከሀገረ ካናዳ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule